TED Talks with Amharic transcript

አሌክ ሶዝ + እስቴሲ ቤከር: ዘላቂ ፍቅር ምን ያመስላል

TED2015

አሌክ ሶዝ + እስቴሲ ቤከር: ዘላቂ ፍቅር ምን ያመስላል
2,253,525 views

እስቴሲ ቤከር ሁሌጊዜም ፍቀረኞችን ለትውውቅ የሚያበቃቸውን አጋጣሚ ታሪክ የማወቅ ጽኑ ፍላጎት ነበራት፡ የፎቶ ግራፍ ባለሙያውን አሌክ ሶዥ ይሄን ታሪክ ለመዳሰስ አንዲረዳት በጠየቀችው ጊዜ እራሷን በአለም ፈጣን ከሚባልለት የፍቅር ትውውቅ መድረክ ላይ አገኘችው ላስ ቬጋስ ውስጥ ያውም በፍቅረኞች ቀን በመቀጠል በኔቫዳ የአረጋውያን ማህበረሰብ በመገኘት ከአሌክ ሶዥ ጋር በመሆን የጥንዶችን ፎቶ መሰብሰብ ያዙ፣ በነዚህ ሁለት ተጻራሪ ውኔታዎች መሀካል በፍቅር ተጣማሪዎች ጥንዶች ከትውውቅ የጋራ ህይወት ወደ መመስረት የሚያሸጋግራቸውን ቁም ነገር አገኙት (ይሄ ንግግር የተዘጋጀው ከፖፕ አፕ መጽሄት ጋር በመተባባር የቴድ 2015 መርሀግብር አካል ሆኖ ነው)

ሜሞሪ ባንዳ: የህጻናት ያለእድሜ ጋብቻ ተከላካይ አርበኚት የትግል ጥሪ

TEDWomen 2015

ሜሞሪ ባንዳ: የህጻናት ያለእድሜ ጋብቻ ተከላካይ አርበኚት የትግል ጥሪ
1,355,672 views

ሜሞሪ ባንዳ የህይወት እጣዋ ከእህቶቿ የተለየ ሆነ እህቷ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወደ ባህላዊው ‹የስልጠና ካንፕ› ተላከች ሴት ህጻናትን ‹ወንድን በጾታ ግንኙነት እንዴት ማርካት እንደሚቻል› የሚሰለጥኑበት ካንፕ በዛም በ11 አመት ጨቅላ እድሜዋ ለእርግዝና ተዳረገች፡፡ ባንዳ ግን ባለመሄድ አቋሟ ጸናች ከዛ ይልቅ ሌሎችን በማደራጀት ለማህበረሰቡ መሪዎች የትኛዋም ሴት ህጻን 18 አመት ሳይሞላት በግዴታ መዳር እንደሌለባት በህግ ደረጃ እንዲጸድቅ ጥያቄ አቀረበች በዚህ አላቆመችም በአገር አቀፍ ደረጃ ትግሏን ገፋችበት.... ለመላው ማላውያን ሴት ህጻናት አመርቂ ውጤትም አስመዘገበች፡፡

ሼይረሺፍ: እጅግ ዋጋው የቀነሰ የኮሌጅ ዲግሪ

TED2014

ሼይረሺፍ: እጅግ ዋጋው የቀነሰ የኮሌጅ ዲግሪ
6,307,713 views

በዪኒቨርስቲ ኦፍ ዘ ፒዩፕል፣ ማንኛውም ሰው የሃይስኩል ዲፕሎማ ካላው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ወይም በኮምፒውተር ሳይንስ በዲግሪ ፐሮግራም ሌሎች ኮሌጆች የሚጠይቁትን የመማሪያ ክፍያ መክፈል ሳይጠበቅባቸው (ለፈተና መፈተኛ ክፍያ ብቻ በመክፈል) መማር ይቻላል:: የዪኒቨርስቲ ኦፍ ዘ ፒዩፕል መስራች የሆኑት ሼይረሺፍ እንደ ሚሉት የከፍተኛ ትምህርት የአሰጣጥ ሂደት እየተለወጠ ነው ማለትም “በፊት ከነበረው የተወሰኑትን ብቻ ተጠቃሚ ከማድረግ የሁሉም ሰው መብት ወደ ማድረግ: በገንዘብ አዋጪ እና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ”::`

ኒሎፈር መርቻንት: ስብሰባ አለቦት? በእግር ይጓዙ

TED2013

ኒሎፈር መርቻንት: ስብሰባ አለቦት? በእግር ይጓዙ
3,297,237 views

ኒሎፈር መርቻንት ቀለል ያለ ነገር ግን ህይወትዎ እና ጤናዎ ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሀሳብ ትሰነዝራለች፡፡ ከግለሰብ ጋር ስብሰባ በሚኖሮት ጊዜ ‹የእግረ መንገድ ስብሰባ› ማካሄድዎን አይዘንጉ እናም ሀሳቦች እየተራመዱ እና እየተነጋገሩ እንዲፈልቁ ይፍቀዱ፡፡

ሪቻርድ ቱሬሬ: ከአንበሶች ጋር ሰላም ያሰፈነ ፈጠራዬ

TED2013

ሪቻርድ ቱሬሬ: ከአንበሶች ጋር ሰላም ያሰፈነ ፈጠራዬ
2,467,150 views

የ13 አመቱ ሪቻርድ ቱሬሬ በሚኖርበት የማሳይ ማህበረሰብ ከብቶች እጅግ ጠቃሚ ሀብቶች ናቸው ይሁንና በተደጋጋሚ በአንበሶች ጥቃት ይደርስባቸዋል በዚህ አጭር መሳጭ ንግግር ታዳጊ ወጣት በፀሀይ ሀይል በሚሰራ የፈጠራው ውጤቱ አማካኝነት አንበሶቹን በፍርሀት በሰላም እንዲሸሹ ሲያደርግ እናያለን

ፓውሎ ካርዲኒ: በአንዴ ብዙ ልስራ ማለቱን ይተዉት፤ ተራ በተራ ለመስራት ይሞክሩ

TEDGlobal 2012

ፓውሎ ካርዲኒ: በአንዴ ብዙ ልስራ ማለቱን ይተዉት፤ ተራ በተራ ለመስራት ይሞክሩ
2,609,537 views

ሰዎች ማብሰል ብቻ አይደለም ትኩረታቸው፤ ያበስላሉ፣ የፅሁፍ መልዕክት ይላላካሉ፣ ስልክ ያወራሉ፣ ዩትዩብ ይመለከታሉ እና የሰሩትን ምርጥ የምግብ ምስል በድር-ገጽ ላይ ይሰቅላሉ፡፡ ዲዛይነሩ ፓውሎ ካርዲኒ ነገሮችን በአንዴ የማስፈጸም ባህላችንን ውጤታማነት ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል እናም ተራ በተራ ነገሮችን ማስፈጸም ላይ ሀሰቦችን ያቀርባል፡፡ ደሳስ የሚሉ የ3ዲ ህትመት ስማርት ስልኮቹ ሽፋናቸው መልስ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

ባንከር ሮይ: ከቤርፉት እንቅስቃሴ እንማር

TEDGlobal 2011

ባንከር ሮይ: ከቤርፉት እንቅስቃሴ እንማር
4,300,944 views

ራጃስትሃን፣ህንድ ሀገር ፥ ምርጥ ትምህርት ቤት አለ ። ማንበብ የማይችሉትን የገጠር ሴቶችንና ወንዶችን የሚያሰለጥን ። በመንደራቸው ውስጥ የፀሀይ ሃይል መሃንዲስ፤ የስነ ጥበብ ሰው፤ የጥርስ ሐኪም እንዲሆኑ የሚየርግ ። ቤርፉት ኮሌጅ (Barefoot College) ይባላል ። መሥራቹ ባንከር ሮይ (Bunker Roy) እንዴት እንደሚሰራ ያስረዳናል።

ዴሬክ ሲቨርስ: ዓላማዎን ለራስዎ ይያዙት

TEDGlobal 2010

ዴሬክ ሲቨርስ: ዓላማዎን ለራስዎ ይያዙት
6,371,544 views

አንድ ምርጥ የህይወት ዕቅድ ሲገለጽልን፤ ደመነፍሳችን በቀጥታ ለሰው እንድናወጋ ነው የሚገፋፋን፡፡ ነገር ግን ዴሬክ ሲቨርስ ዓማን ሚስጥር አርጎ ማቆየት ያዋጣል ነው የሚለን፡፡ ወደ 1920ዎቹ ጊዜ ድረስ በመመለስ እስካሁን ያሉትን ጥናቶች በማየት፤ ግባቸውን ለሰው የሚያጋሩ ግለሰቦች ስኬታማ የመሆን ዕድላቸውን እንደሚቀንሱ ያሳየናል፡፡

ሼሪል ዉዶን (Sheryl WuDunn): የ ዘመናችን ትልቁ ግፍ::

TEDGlobal 2010

ሼሪል ዉዶን (Sheryl WuDunn): የ ዘመናችን ትልቁ ግፍ::
1,194,863 views

የ ሼሪል ዉዶን (Sheryl WuDunn) መጽሐፍ "Half the Sky" ያዓለም ሴቶችን እንግልት የ ሚመረምር ነው:: ታሪኮቿ አስደንጋጭ ናቸው:: ታዳጊ አገሮች ያሉ ሴቶች የትምህርት ና የ ሀብት እኩልነት ሲያገኙ ብቻ ነው ሙሉ የ ሰብአዊ ሀብት የሚኖረን::

ዊልያም ካምክዋምባ: የንፋስን ሀይል እንዴት መጠቀም እንደቻልኩ

TEDGlobal 2009

ዊልያም ካምክዋምባ: የንፋስን ሀይል እንዴት መጠቀም እንደቻልኩ
2,717,871 views

በ14 አመቱ በድህነትና በረሀብ ችግር ውስጥ ያደገው ማላዊው ህጻን ለቤተሰቡ በንፋስ ሀይል የኤሌክትሪክ ማመኝጫ ገነባ፡፡ ዊልያም ካምክዋምባ አሁን በ22 አመቱ ለሁለተኛ ጊዜ በቴድ መድረክ ቀርቦ በራሱ አንደበት ህይወቱን ስለቀየረለት የፈጠራ ስራው ይነግረናል፡፡

አሊሳ ሚለር: ዜና ላይ ያጠነጠነ ዜና

TED2008

አሊሳ ሚለር: ዜና ላይ ያጠነጠነ ዜና
2,182,143 views

የፐብሊክ ራዲዮ ኢንተርናሽናል ሀላፊ የሆነቸው አሊሳ ሚለር ምንም እንኳን ስለዓለም ማወቅ ብንፈልግም፤ የአሜሪካ ሚዲያ ሙሉ ገጽታውን አያሳየንም ትለናለች፡፡ ዓይን ገላጭ ቁጥሮችን እና ምስላዊ ገለጻን በመጠቀም ታስተምረናለች፡፡

ሪቻርድ ሴንት ጆን: 8ቱ የስኬት ሚስጥሮች

TED2005

ሪቻርድ ሴንት ጆን: 8ቱ የስኬት ሚስጥሮች
14,410,517 views

ሰዎች ለምንድ ነው የሚሳካላቸው? ጉብዝናቸው ይሆን? ወይንስ እድለኛ ሆነው? ሁለቱም አይደለም የይለናል የትንታኔ ባለሙያው ሪቻርድ ሴንት ጆን ለአመታት በቃለ መጠይቅ የጥናት ውጤት የደረሰበትን እውነተኛ የስኬት ምስጢር በ3 ደቂቃ አሳጥሮ ያሳየናል፡፡